የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል

20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል “ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለኀብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ ህዳር 29 ቀን በድምቀት የሚከበር ሲሆን በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት እና የኢትዮጽያ ኮሚኒቲ ማህበር ጋር በመተባበር በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የምንኖር ዜጎች አብሮነታችንና አገራዊ አንድነታችን ባማረ መልኩ በሚያሳይ ሁኔታ እና አገራችን ያላትን ውብ ባህልና እሴት በሚያስተዋውቅ መልኩ ህዳር 27 ቀን 2018 ዓ.ም (እ.ኤ.አ ዴሴምበር 06 ቀን 2025) በዱባይ አልማምዛር ፓርክ በድምቀት ይከበራል፡፡

በመሆኑም በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ትውልደ ኢትየጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ በባህላዊ አልባሳት ደምቃችሁ ህዳር 27 ቀን 2018 ዓ.ም (እ.ኤ.አ ዴሴምበር 06 ቀን 2025) ከ 4፡00 PM. ጀምሮ በዱባይ አልማምዛር ፓርክ በመገኘት በዓሉን በጋራ እንድናከብር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት በአክብሮት ይጋብዛል::

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *